አዲስ አበባ | ታህሳስ 30፤ 2016| NBC ETHIOPIA -ዋጋ ጨምረው ሲሸጡ እንዲሁም ባዕድ ነገሮችን በመቀላቀል ለገበያ ሲያቀርቡ በተገኙ 2ሺህ 3መቶ 81 ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገለፀ::
የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ከማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ጋር የግማሽ አመት የእቅድ አፈፃፀም ግምገማ አካሂዷል::
በግምገማው ላይ በቀረበ ሪፖርት በከተማዋ ባለፉት ስድስት ወራት በርካታ ህገ ወጥ እንቅስቃሴዎች መደረጋቸው ተነስቶ የእርምት እርምጃ መወሰዱም ተመላክቷል::
በከተማዋ እየተበራከተ የመጣው ቁማር ቤቶች እየፈጠሩ ያሉትን ማህበራዊ ብሎም ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ለመቆጣጠር ሲባል 4ሺህ 3መቶ 21 ቁማር ቤቶች እንዲዘጉ መደረጉ ተነስቷል::
በህገ ወጥ መልኩ ሲዘዋወር የነበረ ከ85 ሚሊየን በላይ የኢትዮጵያ ብር ጨምሮ የተለያዩ የውጭ ሀገራት ገንዘብ በቁጥጥር ስር መዋሉም ተገልጿል::
ህገ ወጥ ተግባር ሲፈፅሙ ተደርሶባቸዋል በተባሉ 7ሺህ 6መቶ 98 ፔንሲዮኖችን ጨምሮ በርካታ ሆቴሎች እንዲሁም መቃሚያ ቤቶችም ላይ እርምጃ ተወስዷል ተብሏል::
በአክረም ኑርያ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












