አዲስ አበባ | ታህሳስ 26፤ 2016| NBC ETHIOPIA – የሩሲያው ፕሬዝደንት ቬላድሚር ፑቲን በዩክሬን ለሩሲያ የሚዋጉ የውጭ ዜጎች እና ቤተሰቦቻቸው ዜግነት እንዲያገኙ የሚያስችል አዋጅ ላይ መፈረማቸው ተገለጸ፡፡
የውጭ ዜጎች ፖስፖርቱን ለማግኘት ቢያንስ ለአንድ ዓመት የፈረሙበትን ኮንትራት ማሳየት ይጠበቅባቸዋል።
በመደበኛው የሩሲያ ጦር እና መደበኛ ባልሆነ ጦር የተሳተፉ ሁሉ የዚህ መብት ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተገልጿል፡፡
ይህ የፕሬዝደንት ፑቲን እርምጃ የውጊያ ልምድ ያላቸው የውጭ ዜጎች እንዲቀላቀሉ ለማበረታት ያለመ መሆኑ እየተገለጸ ሲሆን ሩሲያ ምን ያህል የውጭ ዜጎች በዩክሬን ውጊያ እንዳሰለፈች ይፋ አልተደረገም።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












