አዲስ አበባ | ጥቅምት 02 2016| NBC ETHIOPIA -ኮሎራዶ ራፒድስ የአርሰናልን የታዳጊ ቡድን አሰልጣኝ ጃክ ዊልሸር ዋና አሰልጣኝ አድርገው ለመሾም ንግግር መጀመራቸው ተዘግቧል።

የሜጀር ሊግ ሶከሩ ክለብ፣ ከ31 አመቱ እንግሊዛዊ ጋር ይፋው ድርድር የጀመረው ከአርሰናል ፈቃድ አግኝቶ እንደሆነ ተመላክቷል።
በባለፈው አመት ጫማውን ከሰቀለ በኋላ፣ የአርሰናል ከ18 አመት በታች ቡድንን የተረከበው ዊልሸር የኤፍ ኤ የታዳጊዎች ዋንጫ የፍጻሜ ተፋላሚ እንደነበር አይዘነጋም። (በዌስትሃም 5-1 ነበር የተሸነፈው።)
የመድፈኞቹ የቀድሞ አማካይ፣ ምንም እንኳን በአርሰናል ቤት ቆይታው ደስተኛ ቢሆንም በ”ሲኒየር” ደረጃ የማሰልጠን እድሉን ካገኘ አይኑን እንደማያሽ ተገልጿል።
በሜጀር ሊግ ሶከር “ዌስት ኮንፈረንስ” የደረጃ ሰንጠረዥ፣ ግርጌ ላይ የሚገኘው ራፒድስ፣ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ነበር ዋና አሰልጣኙን ሮቢን ፍሬሰርን ያሰናበተው።
ኮሎራዶ ራፒድስ፣ በአሜሪካው የአርሰናል ባለቤት ክሮንኬ ስፖርትስና መዝናኛ ድርጅት ስር የሚተዳደር ክለብ ነው።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












