አዲስ አበባ | ጥቅምት 06 2016| NBC ETHIOPIA – በኢትዮጵያ በዶክተር ደረጃ ያሉት የአኒስቴዥያ ባለሙያዎች ቁጥር 200 ያህል ብቻ መሆኑ ተገለፀ::

ዓለም አቀፍ አንስቴዥያ ቀን /World Anesthesia Day / “የማህበረሰብ ግንዛቤ ለአንስቴዥያ ህክምና ደህንነት” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል። ቀኑን በማስመልከትም የጤና ሚኒስትር ከጤና ባለሞያዎችና አጋር አካላት ጋር ውይይት እያካሄደ ነው።
የኢትዮጵያ አኒስቴቲቾች ማህበር ዋና ፀሀፊ ዶ/ር አናኒያ አባተ እንደገለፁት የአኔስቴዥያ ህክምና ከቅድመ ምርመራ እስከ ድህረ ቀዶ ጥገና፤ ታካሚዎች ወደ ትክክለኛው የጤና ሁኔታቸው እስኪመለሱ ድረስ የሚሰጥ ነው ብለዋል

በሀገራችን በዶክተር ደረጃ ያሉት የአኒስቴዥያ ባለሙያዎች ቁጥር 200 ያህል ብቻ መሆኑን ዶ/ር አናኒያ የገለፁ ሲሆን ይህንን ቁጥር ለማሳደግ 8 ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የአንስቴዥያ ባለሞያዎችን እያሰለጠኑ ይገኛል ሲሉ ገልጸዋል ።
በዓለማችን 70 በመቶ ታካሚ ስለ አኔስቴዥያ ህክምና በቂ እውቀት እንደሌላቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ::
የአኔስቴዥያ ቀን /World Anesthesia Day / በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ177ተኛ ጊዜ እየተከበረ ነው።
ሀሴት ሀይሉ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












