አዲስ አበባ | ጥቅምት 02 2016| NBC ETHIOPIA -ቅዳሜ፣ ጥቅምት 03 (Oct 14፣ 2023) የፀሐይ ግርዶሽ ሰሜን ፣ መካከለኛውን እና ደቡብ አሜሪካን ያቋርጣል ። በአሜሪካ ፣በሜክሲኮ ፣በደቡብ እና በመካከለኛው አሜሪካ በሚገኙ ብዙ ሀገራት ውስጥ ይታያል።

በአሜሪካ የፀሐይ ግርዶሽ በኦሪገን ግዛት (Oregon) 9፡13 a.m የሚጀምር ሲሆን በቴክሳስ በ12፡03 p.m ያበቃል።

ቀጥሎም በጓቲማላ፣ ቤሊዝ ፣ሆንዱራስ፣ ኒካራጓ እና ፓናማ ላይ ይታያል። የፀሐይ ግርዶሽ በኮሎምቢያ ወደ ደቡብ አሜሪካ የሚያቋርጥ ሲሆን በአትላንቲክ ውቅያኖስ ደግሞ ፀሐይ ሳትጠልቅ በሰሜን ብራዚል ያልፋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Facebook- https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












