አዲስ አበባ | መስከረም 24 2016| NBC ETHIOPIA – ሆርሞን ከሚያመነጭ እጢ ከሚነሱ ካንሰሮች መካከል የታይሮይድ ካንሰር 95% ይይዛል።

ከታይሮይድ እጢ አራት ዋና ዋና የካንሰር አይነቶች ይነሳሉ። ከነዚህ ውስጥ ሁለቱ ማለትም ፓፒላሪ እና ፎሊኩላር የሚባሉት በህክምናው ዓለም ጥሩ ካንሰሮች እየተባሉ ይጠራሉ።
በጊዜ ከታወቁ እና በኦፕሬሽን ከተወገዱ እነዚህ ካንሰሮች በየትኛውም ታካሚ ላይ የሞት አደጋ አያደርሱም።
ለዚህም ሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች አሉ።
1ኛ የካንሰር ሴሎቹ TSH receptors ያላቸው ማለትም ቲ.ኤስ.ኤች በተባለ ሆርሞን የሚሰሩና በዛም አማካኝነት ሆርሞን የሚያመነጬ በመሆናቸው በመድሃኒት (Levothyroxin) ሴሎቹን ማዳከም ይቻላል። ሌላኛው መንገድ ደሞ የተሰራጬ ሴሎችን በአዮዲን ጨረር ማጥፋት መቻሉ ነው።
2. እጢው በጣም ቀርፋፋ የሆነ እድገት አለው። በዚህም ምክንያት የታይሮይድ ካንሰሩ የመጨረሻ ደረጃ (stage lV) ላይ ቢደርስም እንኳን በኦፕሬሽን በማውጣት የታካሚውን የመዳን እድል መጨመር ይቻላል።
ለታይሮይድ ካንሰር ብቸኛው እና ጥሩ መፍትሄው በቀዶ ጥገና ማውጣት ነው።
የህመሙ ምልክት በምስሉ እንደሚታዩት በአንገት ላይ እብጠቶች ሲሆኑ በሚታዩ ጊዜ በቶሎ ወደ ጤና ተቋም መሄድ እጅግ አስፈላጊ ነው።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook- https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












