አዲስ አበባ | መስከረም 24 2016| NBC ETHIOPIA – በአዲስ አበባ ከተማ በመጪው ቅዳሜ ለሚከበረው የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል ማክበሪያ ስፍራ የጽዳት ዘመቻ ተከናወነ።

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማ አስተዳደሩ ሥራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ በወቅቱ እንደተናገሩት፤ የኦሮሞ ህዝብ ለኢትዮጵያና ለዓለም ካበረከታቸው ሥጦታዎች ውስጥ አንዱ የኢሬቻ በዓል ነው። ይህ በዓል በአዲስ አበባ መከበሩ ቱሪዝምንና የሥራ እድልን አሳድጓል እንዲሁም ውበትነና ድምቀትን ፈጥሯል።
በዓሉን ለማክበርና እንግዶችን ለመቀበል ከተማ አስተዳደሩ የሚጠበቅበት ዝግጅት ማድረጉን ገልፀው፤ እንኳን ለ2016 ኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ብለዋል።
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሙባሪክ ከማል በበኩላቸው፤ ኢሬቻ የአንድነት፣ የሰላምና የፍቅር በዓል ነው። በበዓሉ ሥነ ስርዓትም ጎልቶ የሚታየው ምስጋና ነው ብለዋል።
የቂርቆስ ክፍለ ከተማም በዓሉ ደምቆ እንዲከበር አካባቢውን የማሳመርና የማስዋብ ሥራ መሰራቱን ገልፀዋል።
በጽዳት መርሐግብሩ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማ አስተዳደሩ ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም በጎፈቃደኛ ወጣቶች እና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና አባ ገዳዎች መሳተፋቸውን ኢፕድ ዘግቧል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












