የኢትዮጵያና አውስትራሊያ የሁለትዮሽ ግንኙነት
:: :: :: :: :: ::
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 21/2015 NBC Ethiopia- ኢትዮጵያ ከአውስትራሊያ ጋር ያላትን ለረጅም ጊዜ የቆየ የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር እንደምትሰራ በአውስትራሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሃደራ አበራ ተናገሩ ። አምባሳደር ሃደራ ለአውስትራሊያ ጋቨርነር ጀነራል ዴቪድ ሁርሌይ የሹመት ደብዳቤ አቅርበዋል።
ሁለቱ ባለስልጣናት የሁለቱን አገራት ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት አድርገዋል። በኢትዮጵያና በአውስትራሊያ መካከል ያለውን የረጅም ዘመን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር አበክረው እንደሚሰሩ አምባሳደር ሃደራ ገልጸዋል።
ጋቨርነር ጀነራል ዴቬድ ሁርሌይ የአምባሳደሩ ተልዕኮ የተሳካ እንዲሆን የአውስትራሊያ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አመልክተዋል። እንደ ኢዜአ ዘገገባ ኢትዮጵያ እና አውስትራሊያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን የጀመሩት እ.አ.አ በ1954 ነው።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
