ትራምፕ ምስጢራዊ ሰነዶችን በማጥፋት ተጨማሪ ክስ ቀረበባቸው
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 21/2015 NBC Ethiopia- የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በመኖሪያ ቤታቸው የነበሩትን ሰራተኞች የደኅንነት ካሜራ ምስሎችን እንዲሰርዙ ግፊት አድርገዋል በሚል ሌላ ተጨማሪ ክስ ቀረበባቸው።
እንደ ቢቢሲ ዘገባ ከሆነ በአዲሱ ክስ ዶናልድ ትራምፕ በሶስት ተጨማሪ ወንጀሎች ተከሰዋል ተብሏል ። በዚህም በማራ ላ ጎ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው የነበረው ሰራተኛ ካርሎስ ዲ ኦሊቬራ የክሱ አካል እንደሆነም ታውቋል።
በቶማይ መኮንን










