
የተዘራ የጤፍ ቅንጣት ከሱ በጣም በብዙ እጥፍ የሚከብደውን አፈር ፈንቅሎ ይጐነቁላል፣የግድ ነው፤ ያለዚያ በስብሶ ይቀራል፡፡ አዲስ የተወለደ ጥጃ በተወለደበት ሰዓት ወይንም ደቂቃዎች በእግሩ ቆሞ ወደ እናቱ ጡት ይውተረተራል፣ አማራጭ የለውም፤ ያለዚያ ህይወት አይቀጥልም፡፡ መሆን አለመሆን ነው ምርጫው፡፡ ሰው መሆን ደግሞ ከዚህ በላይ ነው፡፡ ከደመ ነፍስ ያለፈ ነው፣ ሰው መሆን ከእንሰሳዊነት በላይ ነው፣ የስብዕና ልዕቀት፣ የማንነት ከፍታ፣ ዘላለማዊነት…. የሰው መሆን ደመነፍሶች ናቸው፡፡
ሁላችንም ውስጥ የምንመኘው ለማሳካት የምንፈልገውና መሆን የምንሻው ማንነት አለ፡፡ ሰው ከህልሙ ጋር ይፈጠራል፡፡ ለራዕዩ ይኖራል፡፡ መሆን ያለበት እና የሚፈልገውን ሆኖ መገኘት ግን ከህልምና ከምኞት በላይ ነው፡፡ ትጋት፣ ቁርጠኝነት፣ አንዳንዴም መስዋዕትነትን ይጠይቃል፡፡
Support authors and subscribe to content
This is premium stuff. Subscribe to read the entire article.
Login if you have purchased









