

አዲስ አበባ: | ጥር 18 2015 | NBC Ethiopia – ከፖለቲከኞቹ በተጨማሪም ባለስልጣናት ፣የማህበረሰብ አንቂዎች እና የተለያዩ ግለሰቦች የሥለላው ሰለባ ናቸው ተብሏል ፡፡
የብሪታንያ የሳይበር ደህንነት ማዕከል ከተወሰኑ ቡድኖች እና ግለሰቦች መረጃ የመስረቅ ሙከራዎች እየተበራከቱ መምጣታቸውን ተከትሎ አዲስ ማሳሰቢያ ሰጥቷል ፡፡
መረጃ መንታፊዎቹ በሩሲያ እና በኢራን ጉዳዮች ጥናት የሚያደርጉ ዜጎች ላይ ያነጣጠረ ሙከራ እንደሚያደርጉም ተወስቷል፡፡
ማዕከሉ እንደሚለው መረጃ ጠላፊዎቹ ግባቸውን ለማሳካት የማይፈነቅሉት ድንጋይ የላቸውም ፤ርህራሄ ብሎ ነገር አልፈጠረባቸውም፡፡
መረጃውን ለማግኘት የተለያዩ የማታለያ ስልቶችን እንደሚከተሉም ዘገባው ያሳያል ፡፡
ድርጅቶች እና ግለሰቦች ከእንዲህ አይነቱ ጥቃት ራሳቸውን ለማዳን ንቁ ሆነው መጠበቅ እንዳለባቸውም ማሳሰቢያ ተሰጥቷቸዋል ፡፡
ምንም እንኳን የብሪታንያ ባለስልጣናት ሞስኮን እና ቴህራንን በግልጽ ባይከሱም ፤ቢቢሲ ሁለቱ ወገኖች ከእንዲህ ዓይነቱ የሥለላ ተግባር ጀርባ አሉበት ሲል ዘግቧል ፡፡
ኮልድ ሪቨር (Cold River) የተሰኘ የሩሲያ የሥላላ ቡድን ቀደም ሲል በአሜሪካ የኒውክሌር ላቦራቶሪ ላይ እና የተለያዩ ድርጅቶች ላይ ያነጣጠረ የመረጃ ስርቆት ስራ ላይ ተሰማርቷል መባሉ ይታወሳል ፡፡
በተመሳሳይ ቻርሚንግ ኪትን( Charming Kitten) የተሰኘው የኢራን የሥላላ ቡድን በዋሽግተን ፖለቲከኞች ላይ ያነጣጠረ ስለላ ያደርጉ አንደነበር በመረጃው ላይ ተካቷል::









