
አዲስ አበባ |የካቲት 01 2015 | NBC ETHIOPIA በደቡባዊ ቱርክ እና በሰሜናዊ ሶሪያ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከ8,700 በላይ ሆኗል፡፡
የቱርክ የአደጋ መከላከል ባለስልጣን 6,234 ሰዎች ሲሞቱ ቢያንስ 37,011 መቆሰላቸውን አስታውቋል።
በሶሪያ በኩል ደግሞ ቢያንስ ከ2,530 በላይ ሰዎች በርእደ መሬቱ ህይወታቸው ማለፉ ተገልጿል፡፡ በፍርስራሹ ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤተሰቦች በመኖራቸው ቁጥሩ በከፍተኛ ደረጃ ሊጨምር እንደሚችል የዋይት ሄልሜት የነፍስ አድን አገልግሎት ድርጅት አስታውቆዋል፡፡
በቱርክ በፕሬዚዳንት ሬሴፕ ጣይብ ኤርዶጋን በመሬት መንቀጥቀጡ ክፉኛ በተጎዱ 10 ግዛቶች ለሦስት ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጇል።
የአለም ጤና ድርጅት በሰጠው መግለጫ በአደጋው ከ23 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ሊጎዱ እንደሚችሉ አሳውቆዋል። ከ12,000 በላይ የቱርክ ፍለጋ እና አዳኝ ሰራተኞችን ጨምሮ ከ9 ሺ በላይ ወታደሮች በተጎዱ አካባቢዎች እየሰሩ ይገኛሉ፡፡70 ሀገራት የነፍስ አድን ቡድን ሰራተኞች እና እርዳታዎችን አቅርበዋል፡፡









