

አዲስ አበባ |የካቲት 03 2015 | NBC ETHIOPIA-የነፍስ አድን ሰራተኞች አሁንም በሕይወት የተረፉ ሰዎችን ለማግኘት ፍርስራሹን እያሰሱ ነው፣ ነገር ግን ርዕደ መሬቱ ከተከሰተ ዛሬ አምስት ቀናት ያስቆጠረ ሲሆን ሰዎችን በህይወት የማግኝት ተስፋው እየደበዘዘ ነው።
በመላው ቱርክ እና ሶሪያ ከርዕደ መሬት አደጋ የተረፉ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አሁን ላይ በርዕደ መሬቱ ሳቢያ ቤት አልባ ሆነዋል፤የውሃ እና ምግብ ችግር ተጋፍጦባቸዋል።
የዓለም ባንክ በሰጠው መግለጫ ለቱርክ 1.78 ቢሊየን ዶላር እርዳታ ለመስጠት ቃል ገብቷል።ለተጎጂዎቹ ከ70 በላይ ሃገራት፤100,000 እና ከዚያ በላይ የነፍስ አድን ሰራተኞች ድጋፍ እየሰጡ ያለ ቢሆንም የተሽከርካሪ እጥረት እና የተበላሹ መንገዶች በበርካታ የሎጂስቲክስ ችግሮች የተጠበቀውን ያህል ድጋፉ እንደዳይሰጥ አድርጎል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ሃላፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ “ይህ ወቅት የአንድነት ጊዜ ነው፣ ወቅቱ የፖለቲካ ወይም የመለያየት ጊዜ አይደለም ነገር ግን ትልቅ ድጋፍ እንደሚያስፈልገን ግልጽ ነው” ሲሉ አለም አቀፉ ማህበረሰብ ለደረሰው ርዕደ መሬት ተጨማሪ ገንዘብ እርዳታ እንዲያቀርብ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የኋይት ሄልሜትስ የነፍስ አድን ቡድን በክልሉ የደረሰው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍርስራሹ ስር የታሰሩ ሰዎችን ለማስለቀቅ የሚያግዝ ምንም ልዩ መሳሪያ እንዳልያዘ እያሳወቀ ይገኛል።
በርዕደ መሬቱ በቱርክ 18,342 ሰዎች መሞታቸውን እና በሶሪያ ቢያንስ 3,377 ሰዎች መሞታቸው ታውቋል።በሰሜን ምዕራብ ቱርክ በ1999 በደረሰ ተመሳሳይ የመሬት መንቀጥቀጥ 17,000 ሰዎች ሲሞቱ የአሁን ላይ በተከሰተው ርዕደ መሬት የሞቾች ቁጥር በልጧል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) በሕይወት የተረፉ ሰዎች መጠለያ፣ ምግብ፣ ውሃ እና መድኃኒት በጣም በፍጥነት ማግኘት ካልቻሉ ሰብዓዊ አደጋ እንደሚከሰት አስጠንቅቋል።የዓለም ጤና ድርጅት የአውሮፓ የክልል ዳይሬክተር ዶክተር ሃንስ ክሉጅ እንደተናገሩት በሶሪያ ውስጥ ያሉ ማህበረሰቦች ውሃ የሚጠቀሙት ከማጠራቀሚያዎች ነው ይህ ደግሞ ሀገሪቱ ላይ የኮሌራ ወረርሽኝ ሊያጋጥም ይችላል የሚል ስጋት እንዳለ እና ይህም ስጋት ከርዕደ መሬቱ በፊት እንደነበር ገልፀዋል፡፡
መረጃውን ከቢቢሲ እና አልጀዚራ ተጠቅመናል፡፡
በሃና ተሰማ
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት









