፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መጋቢት 21፣ 2016| NBC ETHIOPIA-ሀገራት እንደ መልክዓ ምድር አቀማመጣቸው እና መሬት በፀሃይ ዙሪያ በምታደርገው ዙረት የተለያየ የተፈጥሮ ጸባይን ባልተለመደ መልኩ ያስተናገዳሉ።
አብዛኞቹ ሀገራት እንደየ ወቅቱ ረጅም ቀን፤ አጭር ለሊትን እና አጭር ቀን ረጅም ለሊትን ማስተናገዳችው የተለመደ ነው። ነገር ግን ይህ ክስተት በአንዳንድ ሀገሮች በሌላው የአለም ክፍል እንግዳ በሆነ ሁኔታ ሲፈጠር ይስተዋላል።
ይህም ፖላር ናይት ተበሎ የሚታወቀው 24 ሰአት ጨለማ እና የእኩለ ለሊት ፀሃይ ወይም 24 ሰአት ፀሃይ ሳትጠልቅ የምትቆይበት የተፈጥሮ ክስተት ነው።እንደዚህ አይነት የተፈጥሮ ክስተት የሚስተዋለው አርክቲክ ሰርክል ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ እና በወስጡ የሚገኙ ሀገራት ላይ ሲሆን ምድር በፀሃይ ዙሪያ በመታደርገው ዙረት ፀሃይ በየአመቱ ከአድማሷ ዙሪያ ከፍ እና ዝቅ ስትል የሚከሰት መሆኑን በዘርፉ ላይ ያሉ ባለሞያወች ያስረዳሉ።
ይሄን ክስተት የሚያስተናገዱ ሀገሮች የእኩለ ለሊት ፀሃይ ምድር በሚል ይታወቃሉ ።

የመጀመሪያዋ እንደዚህ አይነት ወቅት የእኩለ ለሊት ፀሐይ እና ሙሉ ቀን ጨለማ የሚከሰትባት ሀገር ኖርዌይ ናት።
ኖርዌይ በእነሱ የወቅት አቆጣጠር በጋ ወራት የጸሃይ መጥለቅ እና መውጣት በተመሳሳይ ሰአት የሚከሰትባት አስገራሚ የተፈጥሮ ጸጋን ተጎናጽፋለች፡፡
ስቫልባርድ የምትባለው የኖርዌይ ከተማ ለረጅም ግዜ ፀሃይ ሳተጠልቅ የምትቆይበት ሲሆን ይህም ከፈረንጆቹ ሚያዚያ 20 እስክ ነሐሴ 22 በየዓመቱ ይቆያል ።
ሌላኛው ፀሐይ የማትወጣበት ወይም ለጥቂት ሰአታት ብቻ ብቅ የምትጠልቅበት ወቅት ሲሆን በዚህ ወቅት ፀሐይ ጥቅምት ጠልቃ እስከ የካቲት አጋማሽ ድረስ ትቆያለች። በነዚህ ወራት ነዋሪው ከሌላው አለም በተለየ በጨለማ ስራ ይሄዳሉ ፤በጨለማ ውስጥም ምሳችውንም ይበላሉ። ይህ ተለመደ ነው በዛች ምድር ፡፡
ቱሪስቶች እንደ ሎፍተን ደሴቶች፣ ሳውዝ ኬፕ እና ትሮምሶ ያሉ የኖርዌይ ከተሞችን በጨለማ የወጣች ጸሃይን እና የእኩለ ቀን ጨለማን ለመመልክት የመጀመሪያ ምርጫችው ያደርጋሉ። ይሄም ኖርዌይን በአለም ረጅሙን ጨለማ እና የማያልቅ ቀን የምታስተናግድ ሀገር አድርጎታል።
ሌላኛዋ በበጋ ወራት ለ72 ቀናት ፀሐይ የማትጠልቅባት እና በክረምት ደግሞ በ ቀን የምትጨለመው በተፈጥሮ ውበቷ እና በማራኪ መልክአ ምድሮች የምትታወቀው ፊንላንድ ናት ።

በአውሮፓ ሰሜናዊ ጫፍ ላይ የሚገኙት የፊንላንድ አርክቲክ ግዛቶች ከዓለም ዙሪያ የሚመጡ ጎብኚዎችን የሚያስደምሙ ገጸ በርከቶችን የተላበሱ ናቸው።
የፊንላንድ ክረምት ወቅት አልቆ በጋ ሲገባ ከረጅሙ የጨለማ ቀናት ወደ እኩለ ሌሊት ፀሃይ ትሸጋገራለች ።
በሰሜናዊው የሀገሪቱ ክፍል ፀሀይ በቀን ለ24 ሰአታት ውብ በሆኑት መልካምድሮች ላይ ደማቅ ብርሃኑዋን ታበራለች ። ማለቂያ የሌለው የቀን ብርሃን ጎብኚወችን የነዚን ከተሞች መልካ ምድሮች ሃይቆችን እና የተለያዩ አካባቢዎችን ያለገደብ እንዲጎበኙ ያስችላቸዋል።

ሌለኞቹ ከሌላው አለም የተለይ የተፈጥሮ ጸጋን የተጎናጸፉት ደግሞ የሩሲያ ከተሞች ናቸው። በሩሲያ የሚገኙ የተለያዩ ከተሞች የቀናቱ እርዝማኔ ይለያይል እንጂ የእኩለ ለሊት ፀሐይን እና ለወራት ፀሐይ ሳትወጣ የምትቆይበትን ወቅት ያስተናገዳሉ። እንደየ አካባቢው ከ86 እስከ 11 ቀናት ረጅም የጨለማ ቀንን ያስተናገዳሉ።
የአሜሪካ ግዛት በሆነችው አላስካ የምትገኘው ኡትኪያግቪክም የዚሁ የተፈጥሮ ክስተት ተካፋይ ናት ።

ከተማዋ በየአመቱ በክረምት ወራት ለ 65 ቀናት ፀሃይ በሰማዩዋ ላይ ሳተታይ ትቆያለች ። በበጋው ወራት ደግሞ 80 የማያቋርጡ ቀኖችን ያሳልፋሉ ።
አየርላንድ ፖላር ናይት ወይም በቀን መጨለም ባይከሰትባትም በክረምት ወራት ግን ማለቂያ የሌለወን ቀን ታስተናግዳለች ።
ከነዚህ ሀገሮች በተጨማሪ ስዊዲን፣ ግሪንላንድ እና ካናዳ በውስን አካባቢዎቻቸው የተፈጠሮ ክስተቱ ይታይባቸዋል፡፡
እነዚ ሀገሮች በክርምት ወራት ላይ አውሮራ ቦሪያሊስ ወይም ሰሜናዊ ብርሃኖች በመባል በሚታወቀው አረንጓዴ ፣ሮዝ እና ወይን ጠጅ ቀለም ያላቸው እንዲሁም በጨለማው ሰማይ ላይ በሚያበሩ ብርሃኖች ይደምቃሉ ፡፡ ይህም ለጎብኚወች አስደናቂ እና አስገራሚ ትእይንትን ይፈጥራል ።
በ-የአብስራ ብርሃኑ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












