በወር አበባ ምክንያት ሴት ተማሪዎችን የሚደርስ ጫና
ሴት ተማሪዎች በወር አበባ ምክኒያት በት/ቤቶች ውስጥ መገልል እንደሚደርስባቸው ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ ፡፡
በሀገራችን ከሚገኙ 51ሺ ት/ቤቶች መካከል ለሴት ተማሪዎች ምቹ የንፅህና መጠበቂያ መሰረተ ልማቶች ያሟሉት 20 በመቶዎቹ መሆናቸው ተገለጸ፡፡
በአለም አቀፍ ደረጃ 300ሚሊዮን የሚሆኑ ሴቶች የንፅህና መጠበቂያ እና ምቹ የመቀየሪያ ስፍራ እንደማያገኙ መረጃዎች ያሳያሉ።









