ዶናልድ ትራንፕ ክስ ሊመሰረትባቸው መሆኑ
በመኖሪያ ቤታቸው በሚገኝ የደህንነት ካሜራ የተቀረጹ ምስሎች እንዲደመሰሱ አድርገዋል በሚል ነው የወንጀል ክሱ የሚመሰረተው፡፡
አቃቢ ህጎች በደህንነት ካሜራው የተቀረጹ ምስሎች የመከላከያ ሚስጥራዊ ሰነዶችን የተመለከቱ መረጃዎች የሚያሳዩ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
የፕሬዝዳንቱ ሁለት ረዳቶች እና ስሙ ያልተጠቀሰ ሰራተኛ ምስሎችን እንዲደመስስ አሲረዋል በሚል የፍትህ ማዛባት ወንጀል ይከሰሳሉ ተብሏል፡፡












