በፈርንሳይ ሊግ ዋን የወቅቱ ሻምፒዮን ፓሪስ ሴንት ዠርሜይ ከ ኦንዤ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።
በፓርክ ዴ ፕሪንስ የሚደረገው ጨዋታ ምሽት 3 ሰአት ከ45 ላይ የሚጀመር ይሆናል። በመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታ በቪቲንሃ ብቸኛ ግብ ኖንትን 1 ለ 0 ያሸነፈው ፒኤስጂ ተከታታይ ድሉን ለማስቀጠል ወደ ሜዳ ይገባል።
በተመሳሳይ ኦንዤም በሊጉ መክፈቻ የመጀመርያ ጨዋታውን የፒኤስጂን ጎረቤት ፓሪስን 1 ለ 0 ማሸነፉ ይታወሳል። የአንድ ቡድን ፍጹም የበላይነት በሚታይበት ሊግ ዋን ባለሜዳው ቡድን የአሸናፊነት ቅድሚያ ግምት ተሰጥቶታል።
በምሽቱ ጨዋታ ከፒኤስጂ በኩል ተከላካዩ ኪምፔቤ በጉዳት ምክንያት የማይሰለፍ ሲሆን፤ ከክለቡ ጋር ውዝግብ ውስጥ የገባው ግብ ጠባቂው ጂያንሉጂ ዶናሩማም ከቡድን ስብስብ ውጪ ተደርጓል።
ሊጉ ቅዳሜ እና እሁድም ሲቀጥል ማርሴይ ከ ፓሪስ፣ ሊዮን ከሜትዝ እና ሊል ከ ሞናኮ የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ይጠበቃሉ።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












