ላሊጋው ምሽት 4፡30 ጅማሮውን ሲያደርግ የአሰልጣኝ ማኑኤል ፔሊግሪኒ ሪያል ቤቲስ በሜዳው ዲፖርቲቮ አላቬስን ያስተናግዳል።
ቤቲስ በመጀመሪያው ሳምንት ከሜዳው ውጪ ተጉዞ ከኢልቼ አቻ ሲለያይ፤ አላቬስ በአንጻሩ በሜዳው ሌቫንቴን አስተናግዶ ድል አድርጓል። በምሽቱ ጨዋታ ከዚህ ቀደም ባለው ሪከርድ ሪያል ቤቲስ የማሸነፍ ቅድመ ግምት ተሰጥቶታል።
ላሊጋው ነገም ሲቀጥል ቀን 8፡30 አትሌቲኮ ማድሪድ በዋንዳ ሜትሮ ፖሊታኖ ኤልቼን ያስተናግዳል። ሻምፒዮኑ ባርሴሎና ከሜዳው ውጪ ተጉዞ ሌቫንቴን ምሽት 4፡30 የሚገጥምበት ጨዋታ ተጠባቂ ሆኗል።
በተመሳሳይ እሁድ ምሽት 4፡30 ከረጅም አመት ወደ ላሊጋው የተመለሰው የሳንቲ ካዞርላው ኦቪዬዶ ሪያል ማድሪድን የሚያስተናግድ ይሆናል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












