:::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::
የቦርንመዙ የግራ መስመር ተከላካይ በበርካታ ክለቦች ይፈለግ የነበረ ቢሆንም በስተመጨረሻ የመርሲሳይዱን ክለብ ለመቀላቀል ወስኗል።
የ21 አመቱ ሃንጋሪያዊ በሚቀጥሉት 48 ሰዓታት የህክምና ሂደቱን አጠናቆ አዲሱ የሊቨርፑል ተጫዋች ይሆናል።
ሚሎስ ኬርኬዝ በአሰልጣኝ አንዶኒ ኢራኦላ በሚሰለጥነው ቦርንመዝ አስደናቂ የውድድር አመት ካሳለፉ ተጫዋቾች አንዱ ነው።
ሻምፒዮኑ ሊቨርፑል በመስመር ተከላካይ ተተኪ ተጫዋቾችን ለማምጣት በወሰነው መሰረት በቀኝ መስመር ተከላከይ ጀረሚ ፍሪምፖንግብ ከባየር ሊቨርኩሰን አስፈርሟል።
የኤንዲ ሮበርትሰን ትክክለኛው ተተኪ ይሆናል በማለትም ሚሎስ ኬርኬዝን የግላቸው ለማድረግ ሂደቱን በማጠናቀቅ ላይ ናቸው።
በ-አልፈሪድ ነስሮ












