ልክ በዛሬዋ ዕለት ግንቦት 27 1876 ዓ.ም የሂዌት ስምምነት ወይም የአድዋ ስምምነት ተብሎ የሚጠራው በብሪታንያ፣ በግብፅ እና በኢትዮጵያ መካከል በአድዋ የተፈረመ ስምምነት ነው።
ይህ ሰምምነት የብሪታንያው ተወካይ በሆነው በአድሚራል ዊሊያም ሂዌት ስም ተሰይሟል፡፡ ስምምነቱ በግብፅና በኢትዮጵያ መካከል ለረጅም ጊዜ ሲንከባለል የቆየውን ግጭት እንዲያበቃ ቢያግዝም በተዘዋዋሪ ግን በኢትዮጵያ እና በኢጣሊያ መካከል አዲስ ግጭት አስነስቷል።
ስምምነቱ 7 አንቀጾች የነበሩት ሲሆን የስምምነቱ ውል በሰሜን ኢትዮጵያ በሚገኘው በኤርትራ ምድር በአሥመራ ከተማ የተካሄደ ሲሆን በግብፅ በኩል በማሰን ቤይ፣ በብሪታንያ በኩል በአድሚራል ዊሊያም ሂዌት፣ በኢትዮጵያ በኩል የኤርትራ ተጠሪ ሆነው በአደራደሩት በራስ አሉላ አማካኝነት ተካሂዷል፡፡
በስምምነቱ ኢትዮጵያ በምፅዋ ወደብ በኩል የጦር መሳሪያን ጨምሮ ሁሉንም እቃዎች በነፃ ለማጓጓዝ እንደምትችል ይደነግጋል። ስምምነቱ ከተጠናቀቀ በኋላ ተወያዮቹ ወደ አድዋ በማምራት ስምምነቱ ለንጉሠ ነገሠቱ አፄ ዮሐንስ አቅርበው ነበር።
ኢትዮጵያ የባሕር በር እንዲኖራት አፄ ዮሐንስ ያቀረቡትን ጥያቄ ወደ ጎን በመተው እንደገና ሌላ የመጨረሻ ያሉትን ስምምነት ሲፈጽሙ፤ የግብፅን እና የእንግሊዝን መብት ይበልጥ የሚያረጋግጥ እና ድል የሚያቀዳጅ ሆኖል። የሂዌት ስምምነት ከፀደቀ በኋላ ብዙም ሳይቆይ በግብፅ ተይዞ የነበረው የምፅዋ ወደብ በእንግሊዝ ይሁንታ ጣሊያኖች እንዲይዙት ተደረገ፡፡
በ- ሔርሜላ ተመስገን
ምንጭ – “የኢትዮጵያ ታሪክ ከ1847 እስከ 1983” በኘሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ












