Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home Analysis

“የኤርትራ ሕዝብ ከኢሳያስ በላይ ጠላት የለውም” – አቶ ጌታቸው ረዳ

“የኤርትራ ሕዝብ ከኢሳያስ በላይ ጠላት የለውም” – አቶ ጌታቸው ረዳ

November 16, 2026
in Analysis, Hard Talk, Politics
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

አቶ ጌታቸው ረዳ የኤርትራ ሕዝብ፣ የሀገሪቱን ሉዓላዊነት ይዘው ወደ መቃብር እየወሰዷት ካሉት ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በላይ ሌላ ጠላት እንደሌለው ተናገሩ።

በኤንቢሲ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ‘ጊዜ ግስ’ መርሐ-ግብር ላይ ቆይታቸውን ያደረጉት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምሥራቅ አፍሪካ አማካሪ ጌታቸው ረዳ፣ ስለ አፍሪካ ቀንድ ጂኦፖለቲካ፣ ስለ ኤርትራ መንግሥት የውስጥ ውድቀት እና ስለ ቀጠናዊ የጥፋት ኃይሎች መዳከም ዝርዝር ትንታኔ ሰጥተዋል።

አቶ ጌታቸው እንደገለጹት የአፍሪካ ቀንድ በዓለም ላይ እጅግ ተለዋዋጭ ከሆኑ እና ግጭቶች በተደጋጋሚ ከሚከሰቱባቸው ቀጠናዎች አንዱ ነው። በተለይም ኢትዮጵያ የምትገኝበት የቀይ ባህር አካባቢ እና የዓባይ ተፋሰስ መነሻነት ለቀጠናው ፖለቲካዊ ብሎም ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ከፍተኛ ትኩረት እንዲሰጠው አድርጓል ነው ያሉት።

በአካባቢው የሚነሱ ቀውሶች በኢትዮጵያ የውስጥ ሰላም ላይ ቀጥተኛ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩ አማካሪው አብራርተዋል። ለአብነትም በሱዳን የተረጋጋ ሰላም እንዲፈጠር ግብጽ ፍላጎት እንደሌላት ጠቁመው፤ ይህም በቀጠናው ላይ የሚፈጥረውን ጫና ተገንዝቦ ጠንካራ የውስጥ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

አክለውም የኤርትራ ፕሬዚዳንት ሀገራቸውን ኤርፖርት፣ መንገድና ፋብሪካ የሌላት ተራ ቦታ አድርገዋታል ሲሉ ገልፀዋል። የሚመሩት መንግስት በተለያዩ መንገዶች የሚያገኘውን ገንዘብ ለኤርትራ ሕዝብ ልማትና ግንባታ ከማዋል ይልቅ፣ ጎረቤት ሀገራትን ለማተራመስ እያዋለው መሆኑንም አጋልጠዋል።

የኤርትራ መንግሥት ራሱ በወጠናቸው እና እርስ በርሳቸው በሚቃረኑ እቅዶች ምክንያት የመፍረስ ዕድሉ እጅግ ሰፊ መሆኑን አቶ ጌታቸው ገልጸው የኢትዮጵያ መከላከያ ታንኮች አስመራ ድረስ መግባት ሳያስፈልጋቸው ሥርዓቱ በራሱ ውስጣዊ ድክመት የሚወድቅበት እድል ሰፊ መሆኑን አስረድተዋል።

በተጨማሪም የኤርትራ መንግሥት ከስህተቱ የመማር አቅሙ እጅግ ዝቅተኛ መሆኑን በመግለጽ ሥርዓቱ አሁንም ‘’የውጭ ኃይሎች ይረዱኛል’’ በሚል የተሳሳተ ስሌት ውስጥ ገብቷል ብለዋል:: ቢሆንም ግን የለኮሰውን እሳት ብቻውን ይቃጠለዋል እንጂ ማንም የሚደርስለት ኃይል አይኖርም በማለት አጽንኦት ሰጥተው ነው የተናገሩት።

“ለኤርትራ አፋሮች ከአስመራ ይልቅ ሰመራ ይቀርባል” ሲሉ የገለጹት አቶ ጌታቸው በኢትዮጵያ እንዲሁም በኤርትራ አፋሮች መካከል ያለውን ጥብቅ ማህበራዊ ትስስር ጠቅሰው፥ የኤርትራ መሪዎች ሕዝቦችን ለያይተው የመግዛት አቅማቸው መዳከሙን አመላክተዋል።

በሌላ በኩል ህብረት ፈጥረው የነበሩ የህወሃት እና የሌሎች የጥፋት ኃይሎች እንቅስቃሴ በውስጣዊ ቅራኔዎች የተሞላ በመሆኑ የህዝብ ድጋፍ በማጣት መፍረሱን አቶ ጌታቸው ገልጸዋል። የሽብር ቡድኑ አመራሮች የሽብር ተግባር ለመፈጸም ጥሪ ቢያደርጉም፣ ስጋት የመሆን አቅም የላቸውም ነው ያሉት።

አሁን ላይ አብዛኞቹ የአመራር አባላት እጅ እየሰጡ መሆናቸውን ጠቁመው፥ የቀሩትም ሾልከው የሚወጡበትን መንገድ እየፈለጉ መሆናቸውን ተናግረዋል። በአንጻሩ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እጅግ የላቀ ዲሲፕሊን እያሳየ መሆኑን አቶ ጌታቸው አድንቀዋል።

በተመሳሳይ ለዳያስፖራው ማህበረሰብ ባስተላለፉት ጥሪ፥ ከነባራዊው እውነታ ጋር በመታረቅ በራሳቸው ቅራኔ ለፈረሱ የጥፋት ኃይሎች ገንዘብ፣ ጊዜና ጉልበት ማባከናቸውን እንዲያቆሙ መክረዋል። በሀገር ውስጥ ያሉ ማናቸውም ጥያቄዎች ካሉ ከፌዴራል መንግሥቱ ጋር በሰላማዊና በሕጋዊ መንገድ ብቻ መነጋገር እንደሚገባም አሳስበዋል።

የአብስራ ተፈራ

Tags: #TPLFEritreaEthiopiaPresident Isaias AfeworkiShaebia
ShareTweetShare
Previous Post

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

Next Post

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Related Posts

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ
#ethiopia

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
7
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ
#ethiopia

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026
15
የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
የኢትዮጵያን እጣፋንታ የሚወስነው ቀይ ባህር
Analysis

የኢትዮጵያን እጣፋንታ የሚወስነው ቀይ ባህር

November 16, 2026
9
ምርኮኞቹ ጀነራሎች ያጋለጡት የህወሓት ሴራ
Analysis

ምርኮኞቹ ጀነራሎች ያጋለጡት የህወሓት ሴራ

November 14, 2026
57
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
50
Next Post
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

የኢትዮጵያን እጣፋንታ የሚወስነው ቀይ ባህር

የኢትዮጵያን እጣፋንታ የሚወስነው ቀይ ባህር

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?