Wednesday, November 18, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home Analysis

ምርኮኞቹ ጀነራሎች ያጋለጡት የህወሓት ሴራ

ምርኮኞቹ ጀነራሎች ያጋለጡት የህወሓት ሴራ

November 14, 2026
in Analysis, Politics
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram


ለሥልጣን ፍላጎት ሲባል የሕዝብን ሕይወት፣ የወጣቶችን ዕጣ ፈንታና የሀገርን ሰላም ለአደጋ ማጋለጥ ምን ያህል ዋጋ ያስከፍላል? በህወሓት በተሳሳተ የጦርነት ስሌት፣ የጋራ ዓላማ የሌለው ጥምረት እና በአመራሩ ስሕተቶች እንዲሁም ራስ ወዳድነት ሳቢያ በሕዝቡ ላይ የደረሰው ጉዳት ከፍተኛ ነው። በመከላከያ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ተዘጋጅቶ የቀረበው «ከሃዲዎቹ ምርኮኞች» የተሰኘው ዘጋቢ ፊልም ፤ ይህንን እውነታ በምርኮኛ ጀኔራሎችና ወጣቶች ምስክርነት አጋልጦታል።

እንደ ሜጀር ጄነራል ዮሐንስ ወልደጊዮርጊስ (ጆን መዲድ) ገለጻ፣ ህወሓት ከሻዕቢያና ከፋኖ ጋር አደረኩኝ ያለው ጥምረት በጋራ ዓላማና በተቀናጀ የጦርነት ስትራቴጂ ላይ የተመሠረተ እንዳልነበረ ጠቅሰው፣ ይልቁንም ኃይሎቹ በአንድ የጋራ ዓላማ ሳይሆን በየራሳቸው ጠባብ ፍላጎት ይንቀሳቀሱ እንደነበር ጠቁመዋል። በጥምረቱ ውጤታማነት ላይ ከመጀመሪያውም ጥርጣሬ እንደነበራቸው የተናገሩት ሌላኛው ከፍተኛ አመራር፣ በወቅቱ የነበራቸው ስጋት አሁን ትክክል ሁኖ እንዳገኙት ተናግረዋል።

ከፋኖ ጋር በተያያዘ ከተሰጣቸው መረጃና በተግባር ባዩት እውነታ መካከል ሰፊ ልዩነት እንደነበር ከፍተኛ መኮነኑ አስታውሰው፣ ፋኖ በግንባር ላይ እንዳለና ከላሊበላ በኩል የሚመጣውን ኃይል እንደሚከላከል ቢነገራቸውም በተግባር ግን የተነገራቸውን ድጋፍ እንዳላገኙ አስታውሰዋል። ይህም በጥምረቱ ውስጥ የመተማመንና የቅንጅት አለመኖር ማሳያ እንደሆነ ጠቅሰዋል።

ስለውጊያው አጀማመር ጀነራል ጆን መዲድ ሲያስረዱ፣ የተጀመረው በጥምረቱ የጋራ እቅድ ቢሆንም፣ ከሦስት ቀናት በኃላ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ባደረገው የጸረ-ማጥቃት እርምጃ (በምዕራብ ትግራይ፣ በሰሜን ምዕራብ እና በሰቆጣ ግንባሮች) ህወሓት መቋቋም አቅቶት በአጭር ጊዜ ዉስጥ ወደ ድንበር ፈርጥጠዋል ነው ያሉት።

አመራሮቹ የጦር ሜዳን ሁኔታ በበቂ ሁኔታ ሳያጠኑ ወደ ጦርነት እንደገቡና በመጨረሻም ሠራዊቱን ወደ ኤርትራ ለማሻገር እንደወሰኑ ጆን መዲድ አስታውሰው፣ አንዳንድ አዛዦችም ለሠራዊቱ ትዕዛዝ ሳይሰጡ በመከላከያ ከበባ ውስጥ እንዳለ ትተውት መሸሻቸውን ተናግረዋል።

የህወሓት አመራር ውሳኔዎችን የሚያሳልፈው በተጨባጭ መሬት ላይ ባሉ ሁኔታዎች ላይ ተመሥርቶ ሳይሆን በስሜታዊነት ብቻ እንደሆነ ልፀው፣ የራሳቸውን የአመራር ድክመት ለመሸፈንም በሌሎች ሰዎች ላይ እንደሚያላክኩ አስታዉሰዋል።

እንደ ጀነራሉ ገለጻ፣ ጦርነቱ የተጀመረው ያለ በቂ ዝግጅትና ባልተመጣጠነ የኃይል ሚዛን ሲሆን፣ በተለይም የፅንፈኛው ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ አመራሮች በኃይል ፍላጎታቸውን ማሳካት እንደሚችሉና ሥርዓቱን መገርሰስ ባይችሉ እንኳ በተሻለ ቁመና ላይ ሁነው መደራደር እንደሚችሉ በማስላት ወደ ጦርነት መግባታቸውን ተናግረዋል። እንዲሁም ይህንን የተቃወሙ አመራሮች አባላትን ሃሳባቸውን በነጻነት እንዳይገልጹ እንደሚያፍናቸው ያስታዉሳሉ።

በመከላከያ ሰራዊት የተማረኩት እንደሚሉት፣ በስሜታዊነት፣ በተሳሳተ የጦርነት ስሌትና በጠባብ የሥልጣን ፍላጎት ላይ ተመሥርቶ የሚወሰድ ማንኛውም እርምጃ መጨረሻው ውድቀትና ኪሳራ መሆኑን ገልፀው፣ ያለ በቂ ዝግጅትና ቅንጅት የሚደረግ ጥምረት፣ እንዲሁም የውስጥ ሐሳብን በማፈን የሚወሰን ኃላፊነት የጎደለው ውሳኔ፣ ሕዝብን ለከፋ ሰቆቃና ወጣቶችን ለአላስፈላጊ መስዋዕትነት እንደሚዳርግ ተናግረዋል።በመጨረሻም ጦርነት አብቅቶ የወደሙ መሠረተ ልማቶች እንዲጠገኑና ወጣቱ ወደ ልማት እንዲመለስ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

Tags: #TPLFEPLFEthiopiaEthiopian defense forceShaebiaTigray
ShareTweetShare
Previous Post

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

Next Post

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

Related Posts

ፋኖ ፀረ-ሰላም ኃይል ነው-የቀድሞው የፋኖ አመራር ማርእሸት ፀሐዩ
Hard Talk

ፋኖ ፀረ-ሰላም ኃይል ነው-የቀድሞው የፋኖ አመራር ማርእሸት ፀሐዩ

November 18, 2026
54
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ
#ethiopia

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
13
የኢትዮጵያን እጣፋንታ የሚወስነው ቀይ ባህር
Analysis

የኢትዮጵያን እጣፋንታ የሚወስነው ቀይ ባህር

November 16, 2026
11
“የኤርትራ ሕዝብ ከኢሳያስ በላይ ጠላት የለውም” – አቶ ጌታቸው ረዳ
Analysis

“የኤርትራ ሕዝብ ከኢሳያስ በላይ ጠላት የለውም” – አቶ ጌታቸው ረዳ

November 16, 2026
23
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
54
ብሔራዊ ጥቅም ማለት መንግስትን መደገፍ አይደለም!
Analysis

ሚዲያዎችና ብሄራዊ ጥቅም

November 11, 2026
22
Next Post
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

“የኤርትራ ሕዝብ ከኢሳያስ በላይ ጠላት የለውም” – አቶ ጌታቸው ረዳ

“የኤርትራ ሕዝብ ከኢሳያስ በላይ ጠላት የለውም” – አቶ ጌታቸው ረዳ

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

ፋኖ ፀረ-ሰላም ኃይል ነው-የቀድሞው የፋኖ አመራር ማርእሸት ፀሐዩ

ፋኖ ፀረ-ሰላም ኃይል ነው-የቀድሞው የፋኖ አመራር ማርእሸት ፀሐዩ

November 18, 2026
በተመድ እውቅና ያገኘው አረንጓዴ አሻራ!

በተመድ እውቅና ያገኘው አረንጓዴ አሻራ!

November 18, 2026
“ማንቸስተር ሁሌም ‘ሰማያዊ’ ሆኖ አይቀጥልም ” ፖቼቲኖ

“ማንቸስተር ሁሌም ‘ሰማያዊ’ ሆኖ አይቀጥልም ” ፖቼቲኖ

November 18, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

ፋኖ ፀረ-ሰላም ኃይል ነው-የቀድሞው የፋኖ አመራር ማርእሸት ፀሐዩ

ፋኖ ፀረ-ሰላም ኃይል ነው-የቀድሞው የፋኖ አመራር ማርእሸት ፀሐዩ

November 18, 2026
በተመድ እውቅና ያገኘው አረንጓዴ አሻራ!

በተመድ እውቅና ያገኘው አረንጓዴ አሻራ!

November 18, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?