February 18, 2026
ከቱርክዬ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶጋን ጋር ዘለግ ያለ ውይይት አድርገናል። ውይይታችን በኢትዮጵያ እና በቱርክዬ መካከል ያለውን ዘላቂ ወዳጅነትና ጠንካራ ትብብር ይበልጥ ያጠናከረ ነው።

በስትራቴጂካዊ የትብብር መስኮች ላይ የሃሳብ ልውውጥ ያደረግን ሲሆን፤ የሁለቱን ሀገራት ጥቅም የሚያስከብሩ አጋርነቶችን ለማሳደግ ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት ዳግም አረጋግጠናል። ዘላቂው ግንኙነታችን ሁለቱ ሀገሮችን የሚያስተሳስረውን ወዳጅነት ይበልጥ እንደሚያጠናክረው ሙሉ እምነት አለኝ።

ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶጋን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBC Ethiopia












