
የብልጽግና ፓርቲ ኦሮሚያ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ማኒፌስቶ እና የምርጫ ምልክት ማስተዋወቅ መርሐግብር አካሂዷል።
በመርሐግብሩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኦሮሚያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ከፍያለው ተፈራ ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ለአፍሪካ ተምሳሌት በዓለም መድረክ ደግሞ አዲስ ሀይል ሆና የምትታይበት ይሆናል ብለዋል።

ፓርቲው የምርጫ ምልክቱ አድርጎ ያቀረበው የስንዴ ነዶ የመደመር፣ የአንድነት፣ የምርታማነትና የሀገር ሉዓላዊነት መገለጫ መሆኑ ተገልጿል።
በመርሐግብሩ ላይ የ ጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሳዓዳ አብዱራህማን፣ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት አወሉ አብዲ፣ የኦሮሚያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ከፍያለው ተፈራን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና ተገኝተዋል።
በ-የአብስራ ብርሃኑ
Source:
@NBCETHIOPIA
Via:
NBC ETHIOPIA












