
በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለመወዳደር የተመዘገቡ የፓለቲካ ፓርቲዎች የመወዳደሪያ ምልክት ማስተዋወቂያና የእጩዎች ሥነ- ምግባር መፈረሚያ መርሀግብር እየተካሄደ ይገኛል።
በመርሀግብሩ 48 ፓርቲዎች የምርጫ መወዳደሪያ ምልክታቸውን አስተዋውቀዋል።
በዚህም መሰረት ፦
1. የመላው ሲዳማ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ፓርቲ :- የምርጫ ምልክት:- በህብረት የተያያዙ እጆች
2. የሲዳማ አንድነት ፓርቲ :- የምርጫ ምልክት:- አውራ ዶሮ
3. የቁጫ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ :- የምርጫ ምልክት:- ቁጫ ቅቤ
4. የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ፓርቲ :- የምርጫ ምልክት:- ልብ
5. የኦሮሞ ነፃነት ግንባር:- የምርጫ ምልክት:- ቦኩ
6. ህብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ :- የምርጫ ምልክት:- አደይ አበባ
7. የወላይታ ብሄራዊ ንቅናቄ :- የምርጫ ምልክት:- ጉላንታ
8. የወለኔ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ :- የምርጫ ምልክት:- ኩራዝ
9. የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ :- የምርጫ ምልክት:- የእጅ ባትሪ
10. ራያ ራዩማ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ :- የምርጫ ምልክት:- በቆሎ
11. አርጎባ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ :- የምርጫ ምልክት:- ብርቱካን
12. የወላይታ ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ :- የምርጫ ምልክት:- ንብ
13. የወላይታ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር:- የምርጫ ምልክት:- አንበሳ
14. የቤኒሻንጉል ህዝብ ነፃነት ንቅናቄ :- የምርጫ ምልክት:- የተጨባበጡ እጆች
15. ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ :- የምርጫ ምልክት:- የተጨበጠ እጅ
16. ህዳሴ ፓርቲ :- የምርጫ ምልክት:- የሞባይል ስልክ
17. የወሎ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ :- የምርጫ ምልክት:- ቁልፍ
18. የኢትዮጵያ ዴሞክራቲክ ፓርቲ :- የምርጫ ምልክት:- ጋሻና ጦር
19. ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት :- የምርጫ ምልክት:- አውራ ጣት
20. የጌዴኦ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት:- የምርጫ ምልክት:- ጎሽ
21. አዲስ ትውልድ ፓርቲ :- የምርጫ ምልክት:- አይን
22. የዶንጋ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት :- የምርጫ ምልክት:- ዝንጅብል
23. ሱማሌ ፌደራሊስት ፓርቲ :- የምርጫ ምልክት:- ግመል
24. የቅማንት ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ :- የምርጫ ምልክት:- ነጭ እርግብ
25. የኩሽ ህዝቦች ብሄራዊ ንቅናቄ :- የምርጫ ምልክት:- የፀሀይ ብርሀን ጮራ
26. የአርጎባ አንድነት ጀበርቲ:- የምርጫ ምልክት:- ጥላ
27. የጉሙዝ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ:- የምርጫ ምልክት:- ማሽላ
28. የአፋር ህዘብ ፓርቲ :- የምርጫ ምልክት:- ቴምር በእጅ
29. የአፋር ነፃ አውጪ ግንባር ፓርቲ :- የምርጫ ምልክት:- ዝሆን
30. ጎጎት ለጉርፔ አንድነት እና ፍትህ ፓርቲ :- የምርጫ ምልክት:- ምሰሶ
31. ዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ :- የምርጫ ምልክት:- የተያያዙ እጆች
32. የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ :- የምርጫ ምልክት:- ሚዛን
33. እናት ፓርቲ :- የምርጫ ምልክት:- ቁልፍ የያዘ እጅ
34. የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ:- የምርጫ ምልክት:- ሰዓት
35. የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ:- የምርጫ ምልክት:- ባለአምስት የእጅ ጣት
36. አንድ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ:- የምርጫ ምልክት:- ዘንባባ
37. ህብረት ለዴሞክራሲ እና ለነጻነት ፓርቲ:- የምርጫ ምልክት:- የእጣን ዛፍ
38. የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር:- የምርጫ ምልክት:- መጽሀፍ
39. ትንሳኤ ሰብዓ አንደርታ ፓርቲ:- የምርጫ ምልክት:- አምባሻ
40. የጋንቤላ ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ:- የምርጫ ምልክት:- አሳ
41. የሐረሪ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ:- የምርጫ ምልክት:- የጀጎል በር
42 ትንሳዔ ስርዓት ቃንጪ ሃቅ:- የምርጫ ምልክት:- ቃንጫ ሀቂ
43. የምዕራብ ሶማሌ ዴሞክራሲ ፓርቲ:- የምርጫ ምልክት:- ፈረስ
45. ሰላም ለኢትዮጵያ ጥምረት:- የምርጫ ምልክት:- የቡና ተክል
46. ብልጽግና ፓርቲ:- የምርጫ ምልክት:- የስንዴ ነዶ
47. የነፃነትና እኩልነት ፓርቲ:- የምርጫ ምልክት:- ብዕር
48. የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሀይል ንቅናቄ :- የምርጫ ምልክት:- መነጽር መሆኑን ፓርቲዎቹ አስታውቀዋል።
በ-ሰላማዊት ወንድወሰን












