
ጉብኝቱን አስመልክተው መልእክታቸውን ያስተላለፉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ:-
“ከክቡር የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ ጋር በ17ኛው መ/ክ/ዘ የተገነባውን የጎንደር ደብረ ብርሃን ሥላሴ ጎብኝተናል።
የጎንደር ዘመንን የሕንጻ አሠራርና አሳሳል የያዘው ይህ ጥንታዊ ሕንጻ፣ ቅርስነቱን ጠብቆ እየታደሰ ነው።
የሚመለከታቸው የክልልና የፌዴራል አካላት እድሳቱ እንዲከናወን ላደረጉት ቅድምና ይመሰገናሉ። እምነት፣ ታሪክና ቅርስ ወዳዶች ሁሉ አስተዋጽዖአችን ይፈለጋል።” ሲሉ በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።
Source:
NBC Ethiopia
Via:
@NBCEthiopia












