የማዕከላዊ ጎንደር ዞን መምሪያዎች ለማዕከላዊ ጎንደር ትምህርት መምሪያ የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል።
መምሪያዎቹ በድምሩ 180 ደርዘን ደብተርና 25 ፖኮ እስክብሪቶ ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን እየተደረገ ያለው የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ለተሻለ የትምህርት ሥራ የሚያነሳሳና አቅም ለሌላቸው ተማሪዎች መልካም መሆኑን የዞኑ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ክንዱ ዘውዱ ተናግረዋል።
ከዚህ ተሞክሮ በመውሰድም ሌሎች ተቋማትና ግለሰቦች ለተማሪዎችና ለትምህርት ቤቶች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል። እየተደረገ ላለው የትምህርት ቁሳቁስም ምስጋና አቅርበዋል።
በርክክብ ፕሮግራሙ የዞኑ ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ገስጥ አሳምናቸው፣ የዞኑ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ክንዱ ዘውዱ እና የዞኑ ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ድግስ መለሰ ተገኝተዋል።
መረጃው የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ነው
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












