በይሮፓ ሊግ አስቶን ቪላ ከ ቦሎኛ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።
በይሮፓ ሊግ የሁለተኛ ቀን ጨዋታዎች ምሽት 4 ሰዓት አስቶን ቪላ በሜዳው ቪላ ፓርክ ቦሎኛን ያስተናግዳል። በውድድር አመቱ ደካማ አጀማመር ያሳየው ቪላ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ከጣሊያኑ ጠንካራ ቡድን ጋር የሚያደርገው ፍልሚያ በመሆኑ ከፍ ያለ ግምት ተሰጥቶታል።
ቪላ ከቀናት በፊት ውጤት ጠፍቷል በሚል የክለቡን ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ሞቺን ከሃለፊነት ማሰነበቱ ይታወሳል። አሁን ላይ እየወጡ በሚገኙ ዘገባዎች ክለቡ የውጤት መጥፋቱ የሚቀጥል ከሆነ አሰልጣኝ ኡናይ ኢምሬንም ሊያሰናብት እንደሚችል እየተዘገበ ይገኛል።
ጫና ውስጥ የሚገኙት ስፔናዊው አሰልጣኝ በምሽቱ ጨዋታ ዮሪ ቴሌመንስ እና አማዱ ኦናናን በጉዳት ሳቢያ ግልጋሎታቸውን አያገኙም። በሌሎች ስታዲየሞች በተመሳሳይ ሰዓት ሊል ከብሬን፣ ሬንጀርስ ከጌንክ፣ ኡትሬክት ከኦሎምፒክ ሊዮን፣ ስቱትጋርት ከ ሴልታ ቪጎ የሚገናኙ ይሆናል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












