የየመን ሁቲዎች እስራኤል ላይ የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት አድርሰው 22 ሰዎች ጉዳት ደረሰባቸው።
የእስራኤል የአደጋ ጊዜ አገልግሎት ሁለት ሰዎች በጠና መጎዳታቸውን አሳውቋል። ጥቃቱ በደቡባዊ እስራኤል ኢላት ከተማ ላይ የደረሰ ከመሆኑም ባሻገር እስራኤል የከፋ አፀፋ ይኖራታል ተብሏል።
የእስራኤል ጦር ሰው አልባ አውሮፕላኑን አየር ላይ ማክሸፍ እንዳልተቻለ ይፋ ያደረገ ሲሆን ቀጠናው ወደ ባሰ ውጥረት ሊገባ ይችላልም ተብሏል። በቀይ ባህር ዳርቻ የተፈጸመው ጥቃት ጉዳት ማድረሱ ሲነገር እካባቢው ላይ ደግሞ ተጨማሪ የፀጥታ ስጋት ሊፈጥር ይችላል ፣የዓለም የንግድ ስርዓትም ይታወካል የሚል መረጃ ተጋርቷል ።
የየመን ሁቲዎች ወታደራዊ ቃል አቀባይ ያህያ ሳሬ “የድሮን ጥቃቱ ዓላማውን አሳክቷል ” ብለዋል። ቢርሼባን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች እና ወታደራዊ መሰረቶች ላይ ጥቃት አድርሰናል በሚልም ያህያ ሳሬ አረጋግጠዋል።
የእስራኤል አየር መከላከያ ስርዓት ለምን ድሮኑን ማክሸፍ እንዳልቻለን እየመረመረ መሆኑንም እሳውቋል።
ዘ ዋሽንግተን ፖስት እንደዘገበው
በ-ቢኒያም ካሴ












