የአርሰናሉ ተጫዋች ኖኒ ማድዌኬ የጉልበት ጉዳት ማስተናገዱ ተነገረ።
የሰሜን ለንደኑ አርሰናል የክንፍ መስመር ተጫዋች ትላንት ምሽት ከማንችስተር ሲቲ ጋር በተደረገው ጨዋታ ጉዳት ማስተናገዱን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል። ማድዌኬ ጨዋታውን በቋሚነት ቢጀምርም ሁለተኛው አጋማሽ ላይ በቡካዮ ሳካ ተቀይሮ መውጣቱ አይዘነጋም።
በጊዜው ጉዳት እንደገጠመው ያልተገለጸ ሲሆን፤ ወደ ሁለተኛው አጋማሽ ከማምራታቸው አስቀድሞ ጉልበቱ ላይ የገጠመው ጉዳት እንዳይባባስ በሚል አሰልጣኙ እንዲቀየር መወሰኑ ተዘግቧል።
መድፈኞቹ 1-1 ተለያይተው ነጥብ በተጋሩበት ጨዋታ ማድዌኬ የመጀመሪያው አጋማሽ ላይ ጥሩ እንቅስቃሴ ቢያደርግም፤ አደጋ እንዳይፈጥር በሲቲ የግራ ተከላካይ ኒኮ ኦራይሊ በሚገባ መያዙ ታይቷል።
የእንግሊዛዊው ተጫዋች ጉዳት የተጋነነ ባይሆንም፤ ለምን ያህል ጊዜ ከሜዳ ሊያርቀው እንደሚችል የተገለጸ ነገር የለም።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












