የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የቀድሞውን የፊሊፒንስ ፕሬዚዳንት በሰብዓዊነት ላይ ወንጀል ፈጽመዋል ሲል ከሰሰ።
ሮዲርጎ ዱተርቴ ሰብዓዊነትን ጥሰዋል ወይንም ከሰብዓዊነት ያፈነገጠ ተግባር ፈጽመዋል በሚል ሶስት ክሶች ተመስርቶባቸዋል። በአደንዛዥ እጽ ላይ ጦርነት ብለው ባወጁበት ሰዓት ቢያንስ የሰባ ስድስት ሰዎችን ህይወት አስቀጥፈዋል በሚል በአይ ሲ ሲ ተከሰዋል የቀድሞው ፕሬዚዳንት ሮዲርጎ ዱተርቴ።
በኒዘርላንድስ ተይዘው የሚገኙት ዱተርቴ 80 ዓመታቸው ሲሆን ከ2013 እስከ 2018 ድረስ ለተፈጸሙ ወንጀሎችም በግላቸው ተጠያቂ ሆነዋል። የመጀመሪያው ከ2013 እስከ 2016 ከንቲባ እያሉ ለተፈጸሙ ወንጀሎች ተጠያቂ ሲሆኑ ሁለተኛውና ሶስተኛው ደግሞ በፕሬዚዳንትነት ዘመናቸው ለፈፀሙት ወንጀል ነው ተብሏል።
የአይ ሲ ሲ መረጃ እንደሚያሳየው ወንጀሉ በፖሊስ እና ፖሊስ ባልሆኑ ሀይሎች የተፈጸመ ነው። ዱተርቴ ሆን ተብሎ ለፖለቲካ ዓላማ የዋለ ውንጀላ ነው በሚል በተደጋጋሚ ሲሞግቱ ቆይተዋል።
ዘገባው የ ዘ ዋሽንግተን ፖስት ነው
በ-ቢኒያም ካሴ












