በፈረንሳይ ሊግ ዋን ኦሎምፒክ ማርሴይ ከፒኤስጂ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።
በ5ኛ ሳምንት ሊግ ዋን በእጅጉ ከሚጠበቁ መርሃግብሮች አንዱ የሆነው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ምሽት 3 ሰዓት ይከናወናል። ማርሴይ የዛሬውን ተጋጣሚ በሜዳው ከማስተናገዱ አስቀድሞ ባደረጋቸው 4 ጨዋታዎች በሁለቱ አቻ ወጥቶ፤ በሁለቱ ድል በማድረግ 6 ነጥብ ይዞ 8ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
በተቃራኒው የአምናው ሻምፒዮን ፒኤስጂ ያደረጋቸውን ጨዋታዎች በሙሉ በማሸነፍ 12 ነጥብ ይዞ ሊጉን በመምራት ላይ ይገኛል። ሁለቱ ቡድኖች ባለፉት አመታት ባደረጓቸውን የርስበርስ ግንኙነቶች ፒኤስጂ ፍጹም ብልጫ ሲወስድ፤ ማርሴይ በተከታታይ በሰፊ የግብ ልዩነት በ7 ጨዋታዎች ሽንፈት ደርሶበታል።
በምሽቱ ጨዋታ በማርሴይ በኩል ጄፍሪ ኮንዶግቢያ እና ሃማድ ትራኦሬ በጉዳት ከቡድን ስብስብ ውጪ ሲደረጉ፤ በተመሳሳይ በፒኤስጂ በኩል ኦስማን ዴምቤሌ፣ ዴዝሪ ዱዌ እና ጆአው ኒቬስ አይሰለፉም ተብሏል።
የሊግ ዋን ኮከብ ግብ አግቢነቱን በ3 ጎሎች እየመራ የሚገኘውም ብራድሊ ባርኮላም ለጨዋታው ላይደርስ እንደሚችል እየተዘገበ ይገኛል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ












