በጣሊያን ሴሪ ኤ ናፖሊ ከ ፒሳ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል። በ4ኛ ሳምንት የጣሊያን ሴሪ ኤ የመጨረሻ ጨዋታ የአምናው ሻምፒዮን ናፖሊ በሜዳው ፒሳን ያስተናግዳል።
3፡45 ሲል በሚጀምረው ጨዋታ ባለሜዳው ናፖሊ የማሸነፍ ሰፊ ግምት ተሰጥቶታል። ናፖሊ እስካሁን ባደረጋቸው 3 ጨዋታዎች በሶስቱም ማሸነፍ የቻለ ሲሆን፤ የተቆጠረበትም አንድ ግብ ብቻ ሆኖ ተመዝግቧል።
በአንጻሩ ወደ ሴሪ ኤው በያዝነው አመት ያደገው ፒሳ እስከሁን ባደረገጋቸው የሊግ ጨዋታዎች በሁለቱ ተሸንፎ፣ በአንዱ አቻ ወጥቶ 1 ነጥብ በመያዝ 19ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ሴሪኤውን ጁቬንቱስ በ10 ነጥብ እየመራ ሲሆን፤ ናፖሊ በምሽቱ ጨዋታ ድል ማድረግ ከቻለ ቦታውን በእጁ ያስገባል።
ሮሜሉ ሉካኩ እና ኮንቲኒ ከናፖሊ፣ ሁዋን ኳዋድራዶ ከፒሳ በጉዳት ሳቢያ ከጨዋታው ውጪ የሆኑ ተጫዋቾች ናቸው።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












