ፋኩንዶ ቦናኖቴ ዳሪዮ ኤሱጆን በመተካት በቼልሲ የቻምፒዮንስ ሊግ የቡድን ስብስብ ውስጥ ተካተተ።
በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ዛሬ ምሽት ከሚደረጉ ጨዋታዎች በጀርመን አሊያንዝ አሬና ስታዲየም ባየር ሙኒክ ከቼልሲ የሚያደርጉት ፍልሚያ ይጠበቃል። ቼልሲ አስቀድሞ ካስመዘገበው የቡድን ስብስብ ውስጥ የክንፍ ተጫዋቹ ዳሪዮ ኤሱጆ መጎዳቱን ተከትሎ ፋኩንዶ ቦናኖቴን መተካቱ ተዘግቧል።
አርጀንቲናዊው ተጫዋች የምዕራብ ለንደኑን ክለብ የተቀላቀለው የዝውውር መስኮቱ ሊዘጋ በተቃረበበት ሰዓት ከብራይተን በውሰት ውል እንደነበር አይዘነጋም። ቦናኖቴ ክለቡ በፕሪምየር ሊግ ካስመዘገባቸው 23 ተጫዋቾች አንዱ ሲሆን፤ ባሳለፍነው ቅዳሜ ከብሬንትፎርድ በተደረገ ጨዋታ የመሰለፍ ዕድል ተሰጥቶታል።
ዳሪዮ ኤሱጆ የገጠመው ጉዳት ለረጅም ጊዜያት ከሜዳ የሚያርቀው በመሆኑ፤ ቦናኖቴ በቋሚነት የቻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎ ያደርጋል ተብሏል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












