ጆዜ ሞሪኒሆ ቤኔፊካን ለማሰልጠን መስማማታቸው ተነገረ።
ፖርቱጋላዊው አወዛጋቢ አሰልጣኝ ሆዜ ሞሪኒዮ ከቱርኩ ክለብ ፌነርባቼ ከሳምንታት በፊት መሰናበታቸው ይታወሳል። ከፖርቱጋል ሚዲያዎች እየወጣ ባለው መረጃ መሰረት ጆዜ ወደ ሃገራቸው በመመለስ ቤኔፊካን ለማሰልጠን ከጫፍ መድረሳቸው እየተዘገበ ይገኛል።
ጆዜ በአውሮፓውያኑ ሚሊኒየም መጀመሪያ ፖርቶን በማሰልጠን የዋና አሰልጣኝነት ህይወት የጀመሩ ሲሆን፣በ2004 ሳይጠበቅ ቡድኑ የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊ በማድረግ ራሳቸውን እንዳስተዋወቁ አይዘነጋም።
ቤኔፊካ በሃገር ውስጥ ውድድር እና በቻምፒዮንስ ሊግ የተዳከመ ውጤት ማመዝገቡን ተከትሎ ባሰናበተው አሰልጣኝ ብሮኖ ላዥ ምትክ ሞሪኒዮን ለመቅጠር መወሰኑ ተሰምቷል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












