የብራዚሉ ፕሬዚዳንት ሉላ ዳሲልቫ ከትራምፕ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለኝም አሉ።
ፕሬዝዳንቱ ይህንን ያሉት ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቃለምልልስ ወቅት ነው። ሉላ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ትራምፕን ሲወቅሱ ቢስተዋሉም አሁን ላይ ይህንን ማለታቸው መሪዎቹ መካከል ያለው ግንኙነት ውይይት ሙሉ ለሙሉ መቋረጡን አመላካች ነው።
ብራዚል የዋሺንግተን ከፍተኛ የንግድ አጋር ብትሆንም ዶናልድ ትራምፕ የ50 በመቶ ታሪፍ መጣላቸው ይታወሳል። የቀድሞው የብራዚሉ ፕሬዝዳንት ጄር ቦልሴናሮን እስር አስመልክቶ ትራምፕ ከፍተኛ ውዝግብ ሲፈጥሩም ከርመዋል።
የታሪፍ ጭማሪውንም ሆነ ፤ ታሪፍ ለመጨመር ትራምፕ ያነሱት የቀድሞ ፕሬዚዳንት የመታሰር ሀሳብ በቀጥታ ፖለቲካ ነው ያሉት ሉላ፤ ትራምፕ ከብራዚል ጋር ባላቸው ግንኙት ለሚሰሩት ስህተቶች ሁሉ የአሜሪካ ህዝብ ይከፍላል ሲሉም አክለዋል።
የብራዚሉ ፕሬዚዳንት ሉላ ደሲልቫም ሆኑ የአሜሪካ አቻቸው ዶናልድ ትራምፕ እስካሁን በቀጥታ ውይይት አድርገው አያውቁም። በትራምፕ የቀደመ አስተዳዳሪነት ጊዜ ስልጣን ላይ አልነበርኩም እርሳቸውም ከቦልሴናሮ እንጂ ከብራዚል ጋር ወዳጅነት አልመሰረቱም ስለዚህ ከእኔም ጋር ምንም አይነት ግንኙነት አይኖራየውም ብለዋል ።
ዘገባው የቢቢሲ ነው
በ-የአብስራ ሚሊዮን












