የኢፌዲሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአራት ዋና ዋና ጉዳዮች በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በዛሬው ዕለት ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥቷል።
መግለጫውን የሰጡት የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው የታላቁ የህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ኢትዮጵያ በዓለም አለማቀፍ ደረጃ የነበራት ፕሎማሲያዊ ግንኙትት ላይ ተጨማሪ ግብዓት ሆኗታልም ሲሉ ሰፋ ያለ ማብራሪያ አድርገዋል።
የግድቡ መጠናቀቅ ከኢትዮጵያውያ አልፎ ለአፍሪካዊያን አዳዲስ የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶችን በአለም አቀፍ ደረጃ የእድል በር የከፈተ አጋጣሚ ተገኝቶበታል ብለዋል።
በዚሁ መግለጫ በአዲስ አበባ የተካሄደው የአፍራሪካ የአየር ንብረት ጉባዔ ላይም ማብራሪያ የሰጡት ቃል አቀባዩ ከ25 ሺህ በላይ ተሳታፌዎች መገኘታቸውን ገልፀዋል። በጉባዔው የኢትዮጵያን ጥቅም የሚያስከብሩ ሰነዶች ተካተዋልም ተብሏል።
በጉባዔው መጨረሻም የአፍሪካ የአየር ንብረት ፈንድ እንዲቋቋምም ከስምምነት መደረሱን የውጭ ጉዳይ መግለጫ አስታውቋል። የአፍሪካ የካረቢያን ማህበረሰብ ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄሄዱ ያስታወሱት ቃል አቀባዩ፤ በዚሁ ጉባዔ አዳዲስ የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንደተመሠረተም ጠቁመዋል።
በተለይም ባርባዶስ ከኢትዮጵያ ጋር የስራ እድል ለዜጎች ለመስጠት ከስራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር መስማማታቸውም ተመላክቷል። በአፍሪካ ካረቢያን ጉባዔ ተሳታፊዎች የታላቁ ህዳሴ ግድብ መመረቁ ኢትዮጵያ የፓን አፍሪካ አርአያነቷን ያስመሠከረችበት ነው ማለታቸው ተገልጿል።
በመጨረሻም በቀጣዩ ሳምንት የተባበሩት መንግስታት ድርጅ (ተ.መ.ድ) 80ኛ ጉባዔውን በኒውዮርክ እንደሚካሄድ ተጠቁሟል። በዚሁ ጉባዔ ላይም ኢትዮጵያም ብሄራዊ ጥቅሟን የሚያስከብሩ አጀንዳዎችን ይዛ ተሳታፊ እንደምትሆን አምባሳደር ነብያት ይፋ አድርገዋል።
በ-እየሩሳሌም ዓለሙ












