የዩታህ ግዛት አቃቤ ህጎች በቻርሊ ከርክ ግድያ የተጠረጠረው ታይለር ሮቢንሰን የሞት ቅጣት እንዲፈረድበት እንጠይቃለን አሉ።
ተጠርጣሪው ለመጀመሪያ ጊዜ በቪዲዮ ፍርድ ቤት የቀረበ ሲሆን ከባድ ወንጀል መፈጸሙን የሚጠቁሙ ማሳያዎችም ተይዘውበታል። ለጥላቻ በቂ ምክንያት አለኝ በሚል ለቤተሰቦቹ እና “ጾታውን ከወንድ ወደ ሴት” ለቀየረው “አጋሩ” ሀሳብ መስጠቱንም ዳኞች አረጋግጠዋል።
አንዳንዶቹ ጥላቻዎች ልድርድርም የሚቀርቡ እንዳልሆነ ተወስቷል። በብዛት የተገኙት ማስረጃዎች ከቤተሰቦቹ እና ጓደኞቹ ጋር ካደረጋቸው ውይይቶች እንደሆነም ተብራርቷል።
የ22 ዓመቱ ተጠርጣሪ በሰባት የህግ ጥሰቶች መወንጀሉም ተነግሯል። በክስ መስማት ሂደቱ ወቅትም ስሙን ከመግለፅ የተሻገረ ድምፅ አላሰማም።
ዘገባው የቢ ቢ ሲ ነው
በ-ቢኒያም ካሴ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












