ማንችስተር ዩናይትድ የሮያል አንተወርፑን ግብ ጠባቂ ሴኔ ላመንስ ለማስፈረም ከስምምነት መድረሱን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።
ቀያይ ሰይጣኖቹ ለዝውውሩ 21 ሚሊየን ዩሮ በቋሚነት እና 4 ሚሊየን ዩሮ ተጨማሪ ክፍያ የሚከፍሉ ይሆናል ተብሏል። ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር በግል ጥቅማ ጥቅማ ለአምስት ዓመት በሚቆይ ውል ከስምምነት መድረስ የቻለው ሴኔ ላመንስ ዝውውሩን ለማጠናቀቅ ጉዞ መጀመሩም ይፋ ተደርጓል።
እንደ ዘ አትሌቲክ ዘገባ አንድሬ ኦናና ክለቡን ካለቀቀ በስተቀር ማንችስተር ዩናይትድ ግብ ጠባቂ የማስፈረም ዋነኛ እቅድ ያልነበረው ሲሆን በመጀመሪያዎቹ ሳምንታት ዩናይትድ ያጋጠመው ውጤት ማጣት ግን የሀሳብ ለውጥ እንዲያመጡ አስገድዷቸዋል።
የ 23 ዓመቱ ሴኔ ላመንስ ባለፈው ዓመት ለቤልጂየሙ ክለብ 44 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ መጫወት የቻለ ሲሆን ክለቡ ለኮንፍረንስ ሊግ ሲያልፍም ትልቅ ሚና መወጣት ችሏል።
በ- ዳንኤል መምሩ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












