በትግራይ ራያ አካባቢ ህገወጡ የህወሃት ቡድና እና አባሪ ወታደራዊ ጀነራሎች በህዝቡ ላይ እያደረሱት ያለው አፈና፣ ግድያ ብሎም ማስፈራራት በቃ ሊባል እንደሚገባ በአዲስ አበባ የሚኖሩ የትግራይ ራያ ተወላጆች ተናገሩ።
ክልሉን እያስተዳደረ የሚገኘው ህገወጥ የህወሓት ቡድን ራስን በራስ የማስተዳደር ዲሞክራሲያዊ ጥያቄ ባለነሳው የራያ ህዝብ ላይ እያደረሱት ያለው ኢሰብአዊ ተግባራት ሁሉም የትግራይ ብሎም የኢትዮጵያ ህዝብ ሊቃወመው እንደሚገባም ተናግረዋል።

ህገወጥ የህውሃት ቡድን እና አንዳንድ ወታደራዊ ጀነራሎች ክልሉን በተለይም ደቡባዊ የትግራይ ዞንን የጦርነት ማእከል ለማድረግና ህዝቡን ወደ ዳግም ጦርነት ለማስገባት እየሞከሩ ይገኛል ሲሉም ገልጸዋል። ይህንን አስነዋሪ ተግባርም የፈደራል መንግስት ጣልቃ በመግባት እርምጃ እንዲወስዱ ነዋሪዎቹ ጠይቀዋል።
የመላው የትግራይ ህዝብ እና በራያ ህዝብ ጥያቄዎች ተመልሰው ወደ ቀድሞ ሰላሙና ልማት እንዲመለስ ትግል ማድረግ እንደሚገባም ተነስቷል።
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












