ከአንድ ዓመት በፊት ወደ ቱርክ ሱፐር ሊግ በማምራት ፌነርባቼን የማሰልጠን ስራቸውን የጀመሩት ጆዜ ሞሪኒሆ በዛሬው እለት ከመንበራቸው መነሳታቸውን ክለቡ ይፋ አድርጓል።
ፌነርባቼዎቹ ከዚህ ውሳኔ የደረሱት ከቀናት በፊት በቤኔፊካ ተሸንፈው በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ሊያሳትፋቸው የሚችለውን ትኬት መቁረጥ ከተሳናቸው በኋላ እንደሆነም ተያይዞ ተገልጷል።
የ 62 ዓመቱ አሠልጣኝ ባለፈው ዓመት ክለቡን ሲረከቡ 45 ሺ ተመልካቾች በፓፓራ ፓርክ ተገኝተው አቀባበል ሲያደርጉላቸው በቴሌቭዥን ቀጥታ ስርጭት 300 ሺ ሰዎች በፌነርባቼ ዩቲውብ 1.9 ሚሊየን ሰዎች ትውውቁን ተከታትለውት ነበር።
ፌነርባቼ በመግለጫው ለጆዜ ሞሪኒሆ መልካሙን ሁሉ ተመኝቷል።
በ ዳንኤል መምሩ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












