ቶተንሃም ኔዘርላንዳዊውን አማካይ ዣቪ ሲመንስ በ 60 ሚሊየን ዩሮ ለማስፈረም ተስማማ።
የባርሴሎናው ላ ማሲያ አካዳሚ ውጤት የሆነው ዣቪ ሲመንስ ዝውውሩን ለማጠናቀቅ በለንደን የሚገኝ ሲሆን የህክምና ምርመራውን ማጠናቀቁንም የ ዘ አትሌቲኩ ዴቪድ ኦርነስቴን ዘገባ ያሳያል።
የ 22 ዓመቱ ተጨዋች አስቀድሞ የምዕራብ ለንደኑን ክለብ ቼልሲ እንደሚቀላቀል ቢጠበቅም በአርቢ ላይብዚህ እና ሰማያዊዎቹ በኩል ከዝውውር ሂሳቡ ጋር በተያያዘ ከስምምነት መድረስ አልተቻለም።
ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በፍጥነት አቅጣጫውን የቀየረው ዝውውሩ አሁን ማረፊያው ሰሜን ለንደን ይመስላል። ሲመንስም መሃመዱ ኩዱስ እና ጆኣኦ ፓሊንሃን በክረምቱ የቶተንሃም አዳዲስ ፍርሚያዎች ዝርዝር ውስጥ ይቀላቀላል።
ቶተንሃም ሆትስፐርስ ከዚህ ቀደም ሞርጋን ጊብስ ኋይት እና ኤብሬቼ ኤዜን ለማስፈረም ሞክሮ እንዳልተሳካለት የሚዘነጋ አይደለም።
በ- ዳንኤል መምሩ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












