ኒውካስትል ዩናይትድ የክለቡን የዝውውር ሪከርድ በመስበር አዲስ አጥቂ ለማስፈረም ተስማምቷል::
ኒውካስትል ዩናይትድ እና ስቱትጋርት በኒክ ቮልትሜድ ዝውውር ዙሪያ ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን ታማኙ የዝውውር ዜና ዘጋቢ ዴቪድ ኦርንስቴይን ዘግቧል።
ማግፓይሶቹ ለአጥቂው ዝውውር በታሪካቸው ከፍለውት የማያውቁትን ገንዘብ እንደሚያወጡ የተዘገበ ሲሆን 65 ሚልዮን ፓውንድ ቋሚ ክፍያ እና እየታየ የሚጨመር 4.3 ሚልዮን ፓውንድ ለመክፈል መስማማታቸው ተገልፆአል።
የ23 አመቱ ተጫዋች ባሳለፍነው አመት ጥሩ ጊዜ ያሳለፈ ሲሆን ለስቱትጋርት በ33 ጨዋታዎች 17 ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።
ተጫዋቹ ለጀርመን ብሄራዊ ቡድን ጥሪ ተደርጎለት በሁለት ጨዋታዎች መሰለፍ የቻለ ሲሆን እንደ አትሌቲክ መረጃ በዚህ ክረምት ከባየርሙኒክ ሶስት የዝውውር ጥያቄዎች ቀርበውለት በክለቡ ስቱትጋርት ውድቅ ተደጎበታል።
ኒውካስትሎች ይህንን ዝውውር ለማጠናቀቅ መቃረባቸውን ተከትሎ በአሌክሳንደር ኢሳክ ዙሪያ አዲስ መረጃዎች ሊደመጡ እንደሚችሉ የሚጠበቅ ሲሆን ሊቨርፑሎች ለስዊድናዊው ተጫዋች ዝውውር 110 ሚልዮን ፓውንድ አቅርበው በማግፓይሶቹ ውድቅ መደረጉ ይታወሳል።
በ-ዘሪሁን አበባው












