የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ከቼክ ብሔራዊ ሙዚየም እና ከቼክ ዲቨሎፕመንት ኤጀንሲ ሀላፊዎች ጋር ስምምነቱን በፕራግ ከተማ በዛሬው እለት ተፈራርመዋል።
ስምምነቱ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ግዜ ህፃናትን ማእከል ያደረገ ዘመናዊ ሙዚየም መገንባት የሚያስችል ሲሆን የቼክ ሪፐብሊክ መንግስት የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርግ ይሆናል። ይህ ቋሚ የልጆች ሙዚየም በወዳጅነት ቁ.2 ፓርክ ውስጥ የሚገነባ ነው።
የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ የህፃናት ሙዚየሙ ህፃናት ቀለል ባለ መንገድ ስለ ሀገራችን ታሪክ እና ባህል እውቀት እንዲኖራቸው ከማስቻልም በላይ በፈጠራ፣ በትምህርትና በእውቀት እንዲጎለብቱ እድል የሚፈጥርላቸው መሆኑን ገልፀዋል።
የቼክ መንግስት ይህንን ሙዚየም ለማቋቋም ለሚያደርገው የገንዘብ እና የቴክኒክ ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል። ይህ ቋሚ የህፃናት ሙዚየም ፕሮጀክት ህፃናት የቱሪዝም ሀብቶቻችንን አውቀው እንዲያድጉ እና በዘርፉ ልማት ላይ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደያበረክቱ የሚያግዝ እንደሆነ ተገልጿል።
መረጃው የቱሪዝም ሚኒስቴር ነው












