የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር ውስጣዊ አንድነትንና ኢኮኖሚያዊ አቅምን ማጠናከር እንደሚገባ የብልፅግና ፓርቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ኃላፊ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር)ገለፁ።
የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽ(አሚኮ) 30ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን አስመልክቶ “መገናኛ ብዙሃን ለብሄራዊ ጥቅምና ለሰላም” በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀ አውደ ጥናት በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው።

የብልፅግና ፓርቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ኃላፊ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) ” ሚዲያ ለብሔራዊ ጥቅም” በሚል ርዕስ በአውደ ጥናቱ ላይ ጥናታዊ ጽሁፍ አቅርበዋል።
በዚህ ጽሁፋቸው እንዳመለከቱት፤ መላው ኢትዮጵያዊ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም በሁለንተናዊ መንገድ ለማስከበር በአንድነት ሊረባረብ ይገባል።
የሀገሪቱን ብሄራዊ ጥቅም የሚጎዳ ማንኛውንም እንቅስቃሴ በሀሳብ የበላይነት መሞገትና ማክሸፍም እንደሚገባ ገልጸው ለዚህም ውስጣዊ አንድነትና ሰላምን በማስጠበቅ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ አቅምን ማጠናከርና የዲሞክራሲ አቅም በመገንባት መረባረብ እንደሚገባ አብራርተዋል።
በአውደ ጥናቱ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ፣ የአማራ ክልል ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ አማረ ሰጤን ጨምሮ ሌሎችም የስራ ሀላፊዎች እየተሳተፉ ሲሆን፤ በቀረቡ ጥናታዊ ጽሁፎች ላይ ውይይት እየተደረገ ይገኛል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።












