የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ-ኡን ጋር ለመገናኘት ፍላጎት እንዳላቸው ገለጹ። ትራምፕ ይህንን የተናገሩት በኦቫል ኦፊስ ከደቡብ ኮሪያ አዲሱ ፕሬዝዳንት ሊ ጄ-ምዩንግ ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው።

ኪም ማግኘት እፈልጋለሁ ያሉት ትራምፕ ፣ በተገቢው ጊዜ ከኪም ጆንግ ኡን ጋር ለመገናኘት በጉጉት እጠባበቃለሁ” ሲሉ ተናግረዋል ። በመጀመሪያ የስልጣን ዘመናቸው ኪምን ሶስት ጊዜ ያገኙት ትራምፕ፣ ከመሪው ጋር መልካም የሚባል ወዳጅነት እንዳላቸውም ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል ።
ትራምፕ በመጀመሪያ የስልጣን ዘመናቸው ያልተሳካውን የኒውክሌር ዲፕሎማሲ እንደገና ለማስጀመር ሲሉ ከሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ-ኡን ጋር ለመገናኘት እንደሚፈልጉ ነው የገለፁት ። ስብሰባውም በዚህ ዓመት ሊሆን እንደሚችል ፍንጭ ሰጥተዋል።
ዘገባው የዘጋርዲያን ነው
በሰላማዊት ወልደገሪማ












