እስራኤል በደቡባዊ የጋዛ ሰርጥ በሚገኘው ናስር ሆስፒታልን ላይ ባደረሰችው ጥቃት ቢያንስ 21 ሰዎች መገደላቸው ተገልጿል ። በጥቃቱ ከሞቱት 21 ሰዎች መካከል አምስት ጋዜጠኞች፣ የህክምና ባለሙያዎች እና የነፍስ አድን ሰራተኞች እንደሚገኙበት ነው የተገለፀው ።
ሰኞ ዕለት በተፈጸመው ጥቃት ለአልጀዚራ፣ ለሮይተርስ እና ለአሶሺየትድ ፕሬስ (AP) የዜና ወኪሎች የሚሰሩ ጋዜጠኞች በጥቃቱ ህይወታቸውን አጥተዋል ።
ከተገደሉት ጋዜጠኞች መካከል የአልጀዚራው መሀመድ ሰላማ፣ የሮይተርስ ካሜራማን ሁሳም አል-መስሪ፣ በወቅቱ ለአሶሺየትድ ፕሬስ (AP) ትሰራ የነበረችው ነጻ ጋዜጠኛ ማርያም አቡ ደቃ፣ እንዲሁም አህመድ አቡ አዚዝ እና ሙዓዝ አቡ ታሃ ይገኙበታል።
ይህ ጥቃት በሃማስና በእስራኤል መካከል ጦርነት ከተጀመረ በሁለት ዓመት ውስጥ፣ እስራኤል በሆስፒታሎች እና በሚዲያ ሰራተኞች ላይ ከፈጸመቻቸው እጅግ ገዳይ ጥቃቶች መካከል አንዱ መሆኑ ተመላክቷል ።
ዘገባው የአልጀዚራ ነው
በ ሰላማዊት ወልደገሪማ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












