በጣሊያን ሴሪ ኤ የሁለተኛ ሳምንት ቀሪ ሁለት መርሃ ግብሮች ምሽት ላይ ሲደረጉ ኢንተር ሚላን ከቶሪኖ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።
ባሳለፍነው የውድድር አመት በመጨረሻዎቹ ሳምንታት ነጥብ ጥሎ ስኩዴቶውን የተቀማው ኢንተር ምሽት 3፡45 ላይ ቶሪኖን በሜዳው ሳን ሲሮ ያስተናግዳል። ሁለቱ ቡድኖች ከዚህ ቀደም ባላቸው የእርስ በእርስ ግንኙነት ኢንተር የበላይነትን በመያዙ በምሽቱም ጨዋታ የአሸነፊነት ቅድመ ግምት ተሰጥቶታል።
ኢንተር አሰልጣኝ ሲሞኒ ኢንዛጊን በክረምቱ ያጣ ሲሆን፤ አዲሱ አሰልጣኝ ክሪስቲይን ኪቩ ምን አይነት ውጤት ያስመዘግባል የሚለው ተጠባቂ ሆኗል።
በምሽቱ ጨዋታ በኢንተር በኩል አማካኙ ሃካን ቻላኖግሉ ባሳለፍነው አመት በተመለከታቸው በርካታ ቢጫዎች ምክንያት አይሰለፍም፤ ሌላኛው አማካኝ ዳቪዴ ፍራቴሲ ከጉዳቱ አገግሞ በቡድን ስብስብ መካተቱ ታውቋል።
ከወሳኙ ጨዋታ አስቀድሞ ምሽት 1፡30 ዩዲኒዜ በሜዳው ሄላስ ቬሮናን ያስተናግዳል።
በ- አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












