በበጀት ዓመቱ 20 የኃይል ማስተላለፊያና ማከፋፈያ ፕሮጀክቶች በዕቅድ ከተያዙ ውስጥ ተካተው ግንባታዎች በተያዘላቸው መርሐ ግብር ሲከናወን መቆየቱን የተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ ገልጸዋል።
በ2017 25423 ጊ.ዋት ለማምረት ታቅዶ 29480 ጊ.ዋት ማመንጨት መቻሉን ዋና ስራ አስፈጻሚው ተናግረዋል። የኢነርጂ ምርት አፈጻጸም 116 በመቶ ማሳካት መቻሉን አንስተው በዚህም ከዕቅድ አንጻር 4100 ጊ.ዋት መመዝገቡንና ከ2016 በጀት ጋር ሲነጻጸር የ43 በመቶ ዕድገት ማሳየቱን አንስተዋል።
በዘርፉ የተከማቸውን ዕዳ ማቃለል መቻሉና ከኤሌክትሪክ ኃይል የተገኘው የውጭ ምንዛሪ ገቢ ማደግ መቻሉ እንዲሁም የተመረተው ኤሌክትሪክ ኃይልን ከማሳደግ አንጻር በ2016 በጀት አመት ከነበረበት 20523 ሜጋ ዋት በ2017 በጀት ዓመት ወደ 28640 ሜጋ ዋት በማሳደግ በ2016 ዓመት ጋር ሲነጻጸር 39.1% ዕድገት ማሰያቱ እንደ ስኬት መመዝገቡን በሪፖርታቸው አቅርበዋል።
በመሰረተ ልማት ላይ የሚደረጉ ስርቆትና በሀገሪቱ ባለው ወቅታው ሁኔታ አንዳንድ አካባቢዎች በዕቅዱ መሰረት ስራዎችን መስራት አለመቻሉ እንደ ችግር ተነስቷል። በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በበጀት ዓመቱ 75.4 ቢሊዮን ገቢ ማግኘቱ ታውቆዋል፡፡
በ-አማኑኤል ምትኩ












