በተያዘው የዝውውር መስኮት ክለቡን መልቀቅ እንደሚፈልግ የተናገረው እና ልምምድ አልሰራም ብሎ ያመጸው ዊሳ ወደ ብሬንትፎርድ የቡድን ስብስብ መመለሱን ቢቢሲ ዘግቧል።
ተጫዋቹ ከአዲሱ አሰልጣኝ ኬት አንድሪውስ ጋር በመነጋገር ሊጀመር በጣት የሚቆጠሩ ቀናት ለቀሩት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ዝግጅት መጀመሩ ተነግሯል። የ28 አመቱ ዊሳ በኒውካስትል ዩናይትድ በጥብቅ እየተፈለገ ሲሆን፣በጥቅል 30 ሚሊዮን ፓውንድ የዝውውር ሂሳብ አቅርቦ በብሬንትፎርድ ውድቅ መደረጉ ይታወሳል።
ብሬንትፎርድ ዊሳን መሸጥ ቢፈልግም የዝውውሩ ሂሳብ አንሷል በሚል እና ተተኪውን ለማምጣት ጊዜው አያመችም በሚል ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል። ይህንን ተከትሎ ቻምፒዮንስ ሊግ መጫወት የሚፈልገው ዊሳ በክለቡ ላይ ማመጹ ታውቋል።
አሁን ላይ ወደ ልምምድ ማዕከሉ ቢመለስም አሁንም ክለቡን የመልቀቅ ፍላጎቱን እንዳልተወ ተመላክቷል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












